አማርኛ

አማርኛ : የሲያትል የሕዝብ ቤተ መጻህፍት ስልታዊ ዕቅድ 2011-2015

Amharic Section

የሲያትል የሕዝብ ቤተ መጻህፍት ስልታዊ ዕቅድ 2011-2015

የሲያትል የሕዝብ ቤተ መጻህፍት በሚቀጥሉት አምስት ዓመታት ውስጥ አገልግሎቶችን እንዴት እንደሚያሻሽል አዲስ ዕቅድ አለው። ያለፈው ዕቅድ ያተኮረው የቤተ መጻህፍቱን ሕንጻዎች የተሻሉ እንዲሆኑ በማድረግ ላይ ነበር።

 

አዲሱ ዕቅድ የተጻፈው በመላው ከተማ ከሚገኙ ተጠቃሚዎች ጋር ውይይት ከተደረገ በኋላ ነበር። ነዋሪዎቹም የጥናት ቅጽ እንዲሞሉ ግብዣ ተደርጎላቸው ነበር። የጥናቱ ቅጽ የታተመውት በእንግሊዘኛ፣ በቻይንኛ፣ በቬትናምኛ፣ በራሻኛ እና በስፓንኛ ነበር። ከ 33,000 በላይ የሚሆኑ ሰዎች የጥናቱን ቅጽ ሞልተዋል፣ እሱም የትኞቹን መጻሕፎች፣ የኤሌክትሮኒክ መረጃና የትምህርት መማሪያዎችን ሰዎች እንደሚወዱ ቤተ መጻፍቱ እንዲያውቅ ረድቶታል።

 

በንግድ ሥራና በትምህርት መስክ ውስጥ ያሉ 18 የመሪዎች ቡድን ለቤተ መጻፍቱ ሹሞች ዕቅዱን በተመለከተ ምክር አቅርበዋል።

 

ለተጨማሪ መረጃ የስልታዊ ዕቅድ አጭር መግለጫን ያንብቡ። pdf

የቤተ፡መፃፍቱ፡ቦታዎች፡ካርታ።
ለነፃ፡የቤተ፡መፃፍቱ፡ካርዶ፡ይመዝገቡ።