አማርኛ

አማርኛ

Amharic Section

የቤተ መጻፍት ተግባር ምንድን ነው?

(What is a library all about?)

 

ቤተ መጸፍት...መጽሐፍ ማንበቢያ፤መማርያ፤ ጓደኞችን ማግኛና፤ መደሰቻ ቦታ ነው።

 

በዩናይትድ ስቲትስ ውስጥ ማንኛውም አካባቢ ወይም ሰፈር ቤተ መጻፍት አለው። ቤተ መጻፍት በአካባቢው ውስጥ ለሚገኝ ማንኛውም ግለሰብ የነጻ አገልግሎት የሚያቀርቡ ቦታዎች ናቸው። ከቤተ መጻፍት መጽሐፎችንና ሙቪዎችን መዋስ ይችላሉ፤ ኢሜይል ለማየት ወይም በኢንተርነት ለመተቀም፤ እንግሊዝኛን፤ ወይም የዜግነት ትምህርት በኮምፒተር ለመማር ኮምፒተርን ይጠቀሙ። እናም ሌሎች ተጨማሪ የነጻ አገልግሎቶች። ለምን? ምክንያቱም የመረጃ ክፍት መሆንና በነጸ መገኘቱ ለሀገራችን ዲሞክራሲ አስፈላጊ እንደሆነ እናምናለን።

 

 

ቤተ መጻፍት ብዙ ሃሳቦች፤መረጃዎች፤ድርጊቶችና አገልግሎቶች የተሞሉበት ነው። በቤተ መጸፍቱ የሚሰሩት ሰራተኞች ደግና ረጂ ሲሆኑ እርሶን ለመርዳት ታጥቀው የተነሱ ናቸው። ለጥያቄዎችዎ መልስ ለመስጠት፤ የሚያስፈልግዎትን አገልገሎቶችና መረጃዎች ለማቅረብ ተዘጋጅተዋል።

 

 

ቤተ መጻፍቱን መጎብኘት የሚያስደስት ነው! እርሶን ለማገልገል 28 ቅርንጫፎች አሉን። አስደናቂዉን የህንጻ አሰራር መጥተው ይመልከቱ። እንድሁም በብዙ ቅርንጫፎች የሚገኙትን የህዝብ የኪነ ጥበብ ስራዎችን፡ እንደ ተናጋሪና ተንቀሳቃሽ ደረጃ( ኢስካሌተር)፤ በግድግዳ ላይ የተሰቀሉትን 120 የሻይ ኩባያዎች፡ በተክሎች የተሽፈነው ጣሪያ የመሰሉትንና ሊገምቱ ከሚችሉት በላይ በቤተ መጻፍቱ የሚያከናዉኑት ብዙ ነገሮች አሉ!

 

የቤተ መጻፍታችን የጊዜ ሰለዳ ፍላጎት በሚያሳድሩ ድርግቶች የተሞላ ሲሆን ትምህርት እየቀሰሙ የሚደሰቱበት ቦታ ነው። ጓደኞችዎንና ጎረቤቶችዎን ይዘው መጥተዉ በሙዚቃ፡ በጭፈራና በሌሎች ባህላአዊ ፕሮግራሞች ይደሰቱ። ምን እንደሚደረግ በተጨማሪ ለማወቅ ከፈለጉ ቀላል ነዉ… ይጠይቁን! ደግሞም ስላሉን ዝግጅቶች በእንግሊዚኛ የኦንላይን የጊዘ ሰሌዳችንን ሊመለከቱ ይችላሉ ወይም በቅርብ ጊዘ ስለሚቀርቡ ዝግጅቶች ዝርዝር በእንግሊዚኛ ሳምንታዊ የጊዜ ሰሌዳ ኢመይል ይመዝገቡ።

 

 

በቤተ መጻፍትዎ ሁሉም ነገር ነጻ ነው!

 

በይበልጥ ለማወቅ ይፈልጋሉ?

 

(Want to know more?)

 

እኝህ በቤተ መጻፍቱ ሊጠቀሙባቸው ከሚችሏቸው ብዙ አገልግሎቶች ውስጥ ጥቂቶቹ ብቻ ናቸው። ጥያቄዎች ካሉዎት ወይም በቤተ መጻፍት መገልገል ለመጀመር አንድ ሰዉ እንዲረዳዎ የሚፈልጉ ከሆነ፡ የቤተ መጻፍቱ ሰራተኞች ሊረዱዎት ዝግጁ ናቸው። እባክዎን በ 206-684-0849 ይደውሉ ወይም በ lew@spl.org ኢመይል ይላኩልን።.

 

ደግሞም የማህበረሰብዎን ማእከል ወይም ዝግጅት ላይ የቤተ መጻፍቱ ሰራተኛ እንዲጎበኙ ጥያቄ ሊያቀርቡ ይችላሉ። ስለ ቤተ መጻፍቱ አገልግሎቶችና ፕሮግራሞች ሊነግሩዎት ይችላሉ ወይም ለቤተ መጻፍት ካርድ እንዲመዘገቡና መጽሃፎችን መዋስ እንዲችሉ ይረዱዎታል። ለጉብኝት ዝግጅት ለማድረግ 206-386-4661 ይደዉሉ።

 

ሌላም ደግሞ የምስራቅ አፍርካ የመጽሃፎችንና ሌሎች ስብሰቦቻችንን ለማየት ማእከላዊ ቤተ መጻህፍትን ወይም የኒዉ ሆሊ ቅርንጫፍን ይጎብኙ።

 

ስለሲያትል የህዝብ ቤተ መጻህፍት ፍላጎትዎ እናመሰግናለን። በዓይን ለመገናኘት በጉጉት እንጠባበቃለን… ወደ ቤተ መጻፍትዎ እንኳን ደህና መጡ!

 

ለሲያትል የህዝብ ቤተ መጻፍት ጓደኞች ለዚህ የቤተ መጻህፍት ማስታወቂያ እርዳታ ገንዘብ ስላቀረቡ ምስጋናችንን እናቀርባለን።

የቤተ፡መፃፍቱ፡ቦታዎች፡ካርታ።
ለነፃ፡የቤተ፡መፃፍቱ፡ካርዶ፡ይመዝገቡ።

ስለ፡ቤተ፡መፃፍትዎ፡የበለጠ፡ይወቁ

(Welcome Video)

 

>።ፊዲዮ፡ይመልከቱ።