The Seattle Public Library

Your Account

March 18, 2018

SPL ድረገጽ ዳግም ንድፎች

SPL ድረገጽ ዳግም ንድፎች | የዳሰሳ ጥናት ውጤቶች

መነሻ

Seattle Public Library ለእርሶ ሲል ድረገጹን ያሻሽላል፡፡ ፍላጎቶትን ለማሟላት እንዲያስችል፣ በቅርቡ የተጠቃሚ ዳሰሳ ጥናት እናካሂዳለን፡፡

የዚህ ዳሰሳ ጥናት ተግባር ድረገጹን አሁን ማን እየተጠቀመ እንዳለና የትኞቹ የመስመር ላይ መርጃዎች ጥቅም እንደሚሰጧቸው ለማወቅ ያስችላል፡፡ ስለ መርጃዎቹ ማን መረጃ እንደሌለውም ለመመልከት ያስችላል፡፡ ይህንን እንደገና ተነድፎ ከሚለቀቀው ጋር ለማወዳደር እንደ መሰረት እንጠቀምበታለን፡፡

ከ 8,000 በላይ ሰዎች የዳሰሳ ጥናቱን አጠናቀዋል፣ ይህም 10 ጥያቄዎችን ይዞ ከጥቅምት 11-25/2016 ድረስ ክፍት ነበር፡፡ ተሳታፊዎች በተለያየ አይነት መንገድ የተመለመሉ ሲሆን ይህም ከቤተ መፃህፍቱ ቅርንጫፍ ቁሶች፣ ከደብዳቤ መልእክት ዝርዝሮች፣ Facebook እና Twitter ማህበራዊ ድረገጾች ላይ በመለጠፍና በ 1>spl.org መነሻ ገጽ ላይ ማስታወቂያ ማድረግን ያጠቃለለ ነበር፡፡ ይህ ማህበረሰቡ በዚህ ፕሮጀክት ላይ ለማሳተፍ ብዙ እድል የሰጠ ነበር፡፡

ግብረመልስ ቅጽ በ spl.org/websiteredesign ላይ "ሀሳቦትን ያጋሩ" የሚለውን በመጠቀም ግብረ መልሶችን መስጠት ይችላሉ፡፡

በሂደቱ ምን እንደተማርን እናሳውቆታለን፡፡ ከታች ያሉት ዝርዝሮች የዳሰሳ ጥናቱ ውጤቶች ናቸው፡፡

 

ቤተ መፃህፍት አጠቃቀም

የመጀመሪያዎቹን ሁለት ጥያቄዎች መልሶች የሚያሳዩት Seattle Public Library መደበኛ - የመስመር ላይ፣ በአካል ወይም በሁለቱም ተጠቃሚ እንደሆኑ ነው፡፡

ወዳሉን ቦታዎች ምን ያህል ግዜ ይመጣሉ?

ይህንን ዳሰሳ ጥናት የወሰዱ 65% ያህሉ ቢያንስ በወር አንዴ ይመጣሉ፡፡

chart with responses for question: ወዳሉን ቦታዎች ምን ያህል ግዜ ይመጣሉ?

የሲያትል የህዝብ ቤተ መፃህፍት ድረገጽን ምን ያህል ግዜ ይጠቀማሉ (spl.org)?

ይህንን ዳሰሳ ጥናት የወሰዱ 75% ያህሉ ቢያንስ በወር አንዴ ድረገጹን ይጠቀማሉ፡፡ ከዛም ከመልሶቹ በመነሳት የድረገጻችን ተጠቃሚዎችን የሚወክለውን ነገር እንድናጠቃልል ያደርገናል፡፡ ተጨማሪ ጥናት አሁን ድረገጻችንን ለማይጠቀሙ ፍላጎቶቻቸው ምን እንደሆነ እንድናውቅ ይረዳናል፡፡

chart with responses for question: የሲያትል የህዝብ ቤተ መፃህፍት ድረገጽን ምን ያህል ግዜ ይጠቀማሉ (spl.org)?

የሲያትል የህዝብ ቤተ መፃህፍት ድረገጽን (spl.org) አዘውትረው ለምን አይጠቀሙም?

ድረገጹን በአመት አንዴ ወይም ከዛ ባነሰ ሁኔታ እንደሚጠቀሙ የመለሱት ለምን አዘውትረው እንደማይጠቀሙ ሦስተኛ ጥያቄ ተጠይቀዋል፡፡ ብዙዎች ‹‹ሌላ›› ብለው የመለሱ ሲሆን፣ እኛ ደግሞ ለምን እንደሆነ ብናውቀው እንወዳለን፡፡ spl.org ለምን እንደማይጠቀሙ መልስ ለመስጠት እባክዎን የግብረ መልስ ቅጹን ይሙሉ፡፡ ከደንበኞቻችን የተሻለ መረዳትን ለማግኘት ከቅርንጫፎቻችን አማካኝነት በአካል ሰዎች እንዴት እንደሚጠቀሙ (ወይም ለምን እንደማይጠቀሙ) ቃለ መጠይቅ ማድረግን ያጠቃለለ ተጨማሪ ጥናት የማድረግ እቅድ አለን፡፡

chart with responses for question: የሲያትል የህዝብ ቤተ መፃህፍት ድረገጽን (spl.org) አዘውትረው ለምን አይጠቀሙም?

ድረገጽ አጠቃቀም

ቀጣዮቹ ሁለት ጥያቄዎች ደንበኞች spl.org ለመጨረሻ ግዜ መቼ እንደጎበኙ እንዲሁም የሚፈልጉትን አግኝተው እንደሆነ ይመለከታል፡፡ በአጠቃላይ፣ አብዛኞቹ የሚፈልጉትን ማመልከት አልቻሉም ነገር ግን የሚፈለገውን በቀላሉ ለማግኘት የሚያስችል መሻሻል ለማድረግ ክፍል ተገኝቷል፡፡

ለመጨረሻ ግዜ spl.org ሲጎበኙ ምክንያትዎ ምን ነበር?

በርካታ የቤተመፃህፍት ተጠቃሚዎች ቦታ ለመያዝ፣ ኢ-መፃህፍትን ለማውረድና ሌሎች አይነት ልውውጦችን ለማድረግ የሚጠቀሙት የመጽሐፍ ዓይነት ዝርዝርን ወይም መተግበሪያዎች ጋር በቀጥታ መስተጋብር እንዳላቸው እናውቃለን፡፡ በቀጣዩ ጥያቄ፣ በ spl.org ስር የሚደረጉ የስራ ዝርዝሮችን አቅርበናል፡፡

ከሌሎቹ ጋር በሚሄድ አምስት ምክንያቶች፤ 80% የሚሆነው ተጠያቂነት መልስ፣ 12% የሚሆነው ደግሞ ‹‹ሌላ›› ብሎ መልሷል፡፡ spl.org እንዴት እንደሚጠቀሙበት ተጨማሪ ነገር ሊነግሩን ከፈለጉ እባክዎ ግብረመልስ ቅጽን ይጠቀሙ፡፡.

spl.org ለመጠቀም ዋና ዋና 5 ምክንያቶች፡-

  1. የቤተ መፃህፍቱን የመስመር ላይ መርጃዎች ለመጠቀም
  2. የቤተ መፃህፍቱን ቦታ መረጃ ለማግኘት
  3. መጽሐፍ ወይም ፊልም ጥቆማዎች
  4. ኢ-መፃህፍቶችና ማውረዶች እገዛ
  5. የቤተመፃህፍቱን ዝግጅቶች ወይም ክፍሎች ፍለጋ

chart with responses for question: ለመጨረሻ ግዜ spl.org ሲጎበኙ ምክንያትዎ ምን ነበር?

የሚፈልጉትን አግኝተዋል?

በአብዛኛው ሰዎች በ spl.org የሚፈልጉትን ያገኛሉ፣ ጥቂት ቦታዎች ላይ ብቻ ከባድ ይሆናል፡- ቤተ መፃህፍቱን ለመገልገል የሚሆን መረጃ፣ የልጆች የቤተ መፃህፍቱን አገልግሎት፣ የስብሰባ ክፍል መያዝ፣ ቅጥር ፈለጋ እገዛ፣ ኢ-መፃህፍቶችን ማውረዶች እገዛ፣ ኢ-መፃህፍቶችን ማውረድ እገዛ እና የቤተ መፃህፍቱን የመስመር ላይ መርጃ መጠቀም፡፡

chart with responses for question: የሚፈልጉትን አግኝተዋል?

የተጠቃሚ ልምድ

የሚቀጥለው ጥያቄ በድረገጹ ላይ የሚኖሩ አጠቃላይ ግንዛቤዎችን ይጠይቃል፣ ይህም በአራት ቦታዎች ላይ ያተኩራል፡- መረጃን ማግኘት ምን ያህል ቀላል ነው፣ መረጃን እንዴት በቀላሉ መረዳት ይቻላል፣ እርዳታና አጠቃላይ ድረገጹ ላይ ያለ ልምድ፡፡ የድረገጹ በእርዳታና አጠቃላይ ልምድ፣ መረጃን ለማግኘትና ለመረዳት እንዴት ቀላል ማድረግ እንደሚቻል ያለ ክፍል ላይ ጥሩ ነጥብ አለው፡፡

በ spl.org ላይ መረጃን እንዴት በቀላሉ ማግኘት ይቻላል?

60% ዳሰሳ ጥናቱን የወሰዱ መረጃን በ spl.org ላይ ማግኘት ቀላል ወይም በጣም ቀላል ነው ብለዋል፣ በጥያቄ 4 ላይ የተሰጡ ምላሾች ጥቂት ቦታዎች ላይ መሻሻል እንዳለበት ተናግረዋል፡፡

ለማግኘት በሚያስቸግሩ መልሶች ላይ በግብረመልስ ቅጹ ላይ ብዙ አስተያየቶችን ተቀብለናል፡-

“መነሻ ገጹ የተዝረከረከና ለማሰስ የሚያስቸግር ነው፡፡ ብዙ መረጃ አለ ነገር ግን ለማግኘት ከባድ ነው፡፡”

“የሆነ ነገር ማግኘት ከባድ ነው ይህም እውቀት የሚፈልግ አልነበረም፡፡ አብዛኛው ነገሮች በብዙ ራስጌዎች/ንኡስ-መድቦች ተደራርበዋል፡፡ ነገሮችን ለማድነቅ ስል የሚያደናቅፍ ነገር አለ፣ ለዛ አላውቅም ነበር ግን የት እንዳገኘሁት ማስታወስ አልችልም፡፡”

chart with responses for question: በ spl.org ላይ መረጃን እንዴት በቀላሉ ማግኘት ይቻላል??

በ spl.org ላይ ያለው መረጃ ለመረዳት ቀላል ነው?

ይህንን ዳሰሳ ጥናት የወሰዱ 75% ያህሉ በ spl.org ላይ ያለውን መረጃ ለመረዳት ቀላል ወይም በጣም ቀላል ነው ብለዋል፡፡

chart with responses for question: በ spl.org ላይ ያለው መረጃ ለመረዳት ቀላል ነው?

በ spl.org ላይ ያለው መረጃ አጋዥ ነው?

ይህንን ዳሰሳ ጥናት የወሰደ ከ 87% በላይ የሚሆኑት በ spl.org ላይ ያለው አጋዥ ወይም በጣም አጋዥ ነው ብለዋል፡፡

chart with responses for question: በ spl.org ላይ ያለው መረጃ አጋዥ ነው?

በአጠቃላይ፣ በ spl.org ላይ ያሎትን ልምድ እንዴት በነጥብ ያስቀምጡታል ?

መጠይቁን ከወሰዱ ከ 75% በላይ ሚሆኑት ልምዳቸው ጥሩ ወይም በጣም ጥሩ እንደሆነ ተናግረዋል፣ ግብረመልስ ቅጻችንን የተጠቀሙ አብዛኛው ሰዎች በተንቀሳቃሽ መሳሪያዎች ላይ ድረገጹ ቀላል እንዲሆን ጠይቀዋል፡፡

“እባክዎን እንደገና የተነደፈውን የቤተ መፃህፍቱን ድረገጽ አቅልሉት (ከመረጃ አጠቃቀምና 3G የማውረጃ ግዜ አንጻር) እና ለተንቀሳቃሽ-የሚስማማ (የሚዋሀድ)”፡፡

“ብዙ ግዜ www.spl.org በአይፎኔ እጠቀማለሁ፣ አሁን ያለው ድረገጽ ለተንቀሳቃሽ ስልክ ተስማሚ አይደለም፡፡”

chart with responses for question:በአጠቃላይ፣ በ spl.org ላይ ያሎትን ልምድ እንዴት በነጥብ ያስቀምጡታል ?

ቋንቋዎች

ደንበኞቻችን የሚጠቀሟቸውን ቋንቋዎች በተሻለ ሁኔታ ለመረዳት በምናደርገው ጥረት፣ የዳሰሳ ጥናቱ በቋንቋ ላይ ብዙ ጥያቄዎችን ይዟል፡፡ በተጨማሪም፣ የዳሰሳ ጥናቱ በሰባት ቋንቋዎች ይገኛል፡- እንግሊዘኛ፣ አማርኛ፣ ቻይንኛ፣ ሩሲያኛ፣ ሶማልኛ፣ ስፓኒሽና ቬትናምኛ ይገኛል፡፡ ከማህበረሰቡ ጋር በጥምረት የሚሰራ ሰራተኛ ማህበረሰቡ ጋር የሚደርሰው ኢንግሊዝኛን እንደ ሁለተኛ ቋንቋ ከሚናገሩ ጋር ነው፤ነገር ግን የዳሰሳ ጥናቱ የሚደረገው የእንግሊዝኛ ቋንቋን እንደመጀመሪያ የመግባቢያ መንገድ መበጠቀም ነው፡፡

ከ 90% በላይ ምላሽ ሰጭዎች ድረገጹ በእንግሊዝኛ መሆኑ በጣም ምቾት የሚሰጣቸው ሲሆን 5% የሚሆኑት ደግሞ በተወሰነ መልኩ ምቾት ይሰጣቸዋል፡፡ 1% የሚሆኑት ደግሞ በነዚህ ገጾች የማይመቻቸው ወይም ከነጭራሹ የማይመቻቸው ናቸው፡፡

የእንግሊዘኛ ቋንቋ መጠቀም ምን ያህል ይቀልዎታል?

መጠይቁን ከወሰዱ ከ 90% በላይ ምላሽ ሰጭዎች በ spl.org ላይ ያሉ ገጾች እንግሊዘኛ ቋንቋ መያዛቸው ምቾትን እንደሚሰጣቸው ተናግረዋል፡፡ ምንም እንኳን፣ 1050 ሰዎች (13%) በቤታቸው ከእንግሊዘኛ ሌላ ቋንቋ እንደሚጠቀሙ ተናግረዋል፡፡

እንዲሁም በይዘቶቹ ወሳኝነት ላይ ብዙ አስተያየቶችን ተቀብለናል፡-

“በድረገጹ ላይ መሻሻሎችን ማድረግ፣ የእንግሊዝኛ ቋንቋ ችግር ያለባቸውን የበለጠ የሚያግዝ ስለሆነ የተወሰነ ገንዘብ ማውጣት ያስፈልጋል ብዪ አስባለሁ፡፡ ”

"“ድረገጹ በተለያየ አይነት ቋንቋ እንዲታይ እፈልጋለሁ፣ ከተለያየ ሀገር የመጡ ሰዎች በከተማው አሉን፡፡”

chart with responses for question: የእንግሊዘኛ ቋንቋ መጠቀም ምን ያህል ይቀልዎታል?

በራስ ተርጓሚው ምን ያህል ያግዛል?

ስለ በራስ ተርጓሚው መሣሪያው ስንጠይቅ፣ 80% ያህል መላሾቹ እነዚህ መሳሪያዎች በጣም አጋዥ ወይም በተወሰነ መልኩ አጋዥ.

chart with responses for question: በራስ ተርጓሚው ምን ያህል ያግዛል?

የሚረዱ መሳሪያዎችን መጠቀም

የማየት፣ የመስማት፣የአእምሮ ወይም በተሽከርካሪ ጉዳት ችግር ያለባችው ድረ ገጹን እንዲጠቀሙ እንዴት ልንረዳቸው እንደምንችል ማወቅ እንፈልጋለን። ኢንተርኔት ለመጠቀም የቴክኖሎጂ እርዳታ እንደሚፈልጉ ጠይቀን 1.2% መልሰዋል አዎ፡፡ 1.2% የሚሆኑት ምላሽ አላውቅም ነው፡፡ ስርጭትና የዳሰሳ ጥናት ንድፉ ምድብ ዝቅተኛ መልስ ጠብቀን ነበር፡፡ የተሻለ የተናጠል ተደራሽነት እንዲኖር በ Library Equal Access Program ላይ በመስራት ተጨማሪ ጥረቶችን እናደርጋለን፡፡

ምንድነው የሚቀጥለው

በጥር 2017፣ የንድፍ ቡድናችን (Domain 7) መዋቅረ ኮምፒውተርንና ንድፍ ስራዉን ይጀምራል፡፡ ይህ ተግባር በድረገጹ ላይ መረጃን እንዴት ማደራጀት እንደሚቻል ለማወቅ ይረዳል፡፡ የዳሰሳ ጥናቱ ከብዙዎቹ አንዱ የጥናት መሳሪያ ሲሆን በሂደቱ ላይ ለምንወስደው ውሳኔ ይረዳል፡፡

ተጨማሪ ጥናቶች ላይ ለመሳተፍ ከፈለጉ፣ እባክዎን በዚሀ ቅጽ በመጠቀም ያሳውቁን እንዲሁም ኢሜል አድራሻዎ መካተቱን እርግጠኛ ይሁኑ፡፡

spl.org/websiteredesign በመጎብኘት ስለ ደረገጹ ዳግም ንድፎች የቅርብ ግዜ መረጃዎችን ማግኘት ይችላሉ፡፡ እንዲሁም እባክዎ ድረገጹ ላይ ባለ ማስፈንጠሪያ “ሀሳቦትን ያጋሩ”፡፡ እየሰማን ነው፡፡

share your thoughts